ኡስታዝ የቁርአን መማሪያ

10 Tsg.+
Downloads
Altersfreigabe
PEGI 3
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot
Screenshot

Über diese App

ኡስታዝ የቁርአን መማሪያ

መተግበሪያው ቁርአንን መማር ለሚፈልግ ለመማር ምቹ እና ለውጥ ማምጣት የሚችል እንዲሆን ተደርጎ በክፍሎች ተከፋፍሎ የተዘጋጀ ምቹ መተግበሪያ ነው።
ከመሰረታው የዐረብኛ ፊደላት ጀምሮ እስከ ቁርአን ድረስ በውስጡ አካቶ ይዟል።

መተግበሪያ ከያዛቸው ይዘቶች መካከል
ክፍል አንድ
* ስለ ዓረብኛ ፊደላቶች በስፋት የሚዳሰስበት ክፍል ሲሆን በውስጡ
- የዐረብኛ ፊደላትን በድምጽ ከመልመጃ ጋር
- የፊደላትን ድምጽ አዎጣጥ የሚያስተምር ለሁሉም ፊደሎች ምስል እና ቪዲዮዎች
- ፊደላት በቃላት ውስጥ በተለያየ ቦታ ሲመጡ ያላቸውን ቅርጽ ከመልመጃ ጋር አካቶ ይዟል።

ክፍል ሁለት
* ስለ አናባቢዎች እና መሳቢያዎች ዝርዝር ትምህርቶችን የያዘ ክፍል ሲሆን
- መሰረታዊ አናባቢዎችን ፈትሃ ፣ ዶማ እና ከስራ በድምጽ እና በጽሁፍ
- ተንዊን (ፈትሃተይን ፣ ዶመተይን እና ከስረተይን ) በጽሁፍ እና በድምጽ
- የመሳቢያ ፊደላቶች (አሊፍ ፣ ያ እና ዋው) በጥሁፍ እና በድምጽ
- ሸዳህ ለሁሉም አናባቢዎች እና ተንዊን በጽሁፍ እና በድምጽ

ክፍል ሶስት
* ይህ ክፍል ቃላቶችን ማንበብ የምንለማመድበት ክፍል ሲሆን ከቀላል ቃላቶች ነጣጥሎ ከማንበብ እስከ አያይዞ ማንበብ ድረስ በጽሁፍ እና በድምጽ

ክፍል አራት
* ይህ ክፍል ቃላቶችን መመስረት የምንለምመድበትን ኪቦርድ የያዘ ክፍል ሲሆን በዚህ ኪቦርድ ቃላቶች በዓረብኛ በመጻፍ በአማርኛ ንባቦችን ምን እንደሆነ ቀጥታ የሚያሳየን ኪቦርድ ነው።

ክፍል አምስት
* በዚህ ክፍል ላይ ቁርአንን ማንበብ የምንጀምርበት ክፍል ሲሆን ቁርአንን አያት በአያት ነጥጥለን እንዲሁም ሙሉ ሱራው በአንድ ጊዜ ማዳመጥ የምንችልበትን መንገድ ይዟል።
- ቁርአኑን ካዳመጥን በኋላ የራሳችንን አቀራር ለመፈተሽ ሌላ መተግበሪያ ሳያስፈልገን እዚያው ላይ ድምጻችንን በመቅረጽ ምዳመጥ እንችላለን።

ክፍል ስድስት
* በዚህ ክፍል ውስጥ መሰረታዊ የሆኑ የተጅዊድ ህጎችን የምንማርበት ክፍል ሲሆን በቁርአን ውስጥ በስፋት የሚገኙትን እና እንደመነሻነት የሚያስፈልጉንን የተጅዊድ ህጎች ከድምጽ ምሳሌዎች ጋር ይዟል።
ትምህርቱን ውጤታማ ለማድረግ ተማሪው ከአንድ ክፍል ወደሌላ ክፍል ለምለፍ በክፍሉ ውስጥ የተዘጋጀውን ማጠቃለያ ፈተና በመፈተን የሚጠበቅበትን ውጤት ማምጣት ይኖርበታል።

መተግበሪያውን ሙሉ ለሙሉ ለመጠቀም መመዝገብ ስለሚፈልግ እዚያው መተግበሪያው ውስጥ መመዝገቢያውን በመጠቀም መመዝገብ እና ሙሉ ትምህርቱን መማር ይችላሉ።

ስለመተግበሪያው ያለዎትን አስተያየት ከትልቅ ምስጋና ጋር እንቀበልላለን።
አስተያየትዎትን መተግበሪያው ላይ ባለው የቴሌግራም አካውንት ይላኩልን።

አላማችን ዘመናዊ የቁርአን መማር መንገዶችን በመፍጠር ሁሉም ቁርአንን እንዲማር ማስቻል ነው። ለዚህም አስተያየታችሁ ለአላማችን ትልቅ አበርክቷችሁ ነው።

መልካም ትምህርት....
Aktualisiert am
14.04.2025

Datensicherheit

Was die Sicherheit angeht, solltest du als Erstes verstehen, wie Entwickler deine Daten erheben und weitergeben. Die Datenschutz- und Sicherheitspraktiken können je nach deiner Verwendung, deiner Region und deinem Alter variieren. Diese Informationen wurden vom Entwickler zur Verfügung gestellt und können jederzeit von ihm geändert werden.
Keine Daten werden mit Drittunternehmen oder -organisationen geteilt
Hat sich verpflichtet, den Google Play-Richtlinien für familienfreundliche Inhalte zu folgen

Neuerungen

* New UI In Some Places
* Font Size Issue Fixed
* More Explanations Added For Each Topic