ለአማርኛ የመጀመሪያው ፣ ይህ መተግበሪያ በ50,000 ቃላት እና በ5,000 ምሳሌያዊ አባባሎች ማለቂያ ፊደላት የሚገኙትን አናባቢና ተነባቢ የድምፅ ስራዓተ ጥለቶች የሚለይ ነው። በፍለጋ ሳጥን በምናስገባቸው (ቃላት ወይ ነጠላ ፊደላት) አማካኝነት ፣ ስልተ-ምት ያላቸውን ቃላት እና አባባሎችን ይዘረዝራል፡፡
የሚገጥሙ ቃላቶችን እና አባባሎችን ፍለጋ ፣ ከትውስታ ማህደር / ከአዕምሮ መሆኑ ቀረ።
ከእንግዲህ ወዲያ ፣ ቤት የሚመቱ ቃላት እና ምሳሌያዊ አባባሎቸ በበረከቱ ይገኛሉና ፣ የግጥም ፅሁፍ ትኩረት ወደ መልዕክቱ ትርጉም / ወደ ጥልቀቱ የማዘንበሉ ሁኔታ ይኖራል።
ምሳሌያዊ አባባሎችንም በሚመለከት - ግጥምጥም ፣ አሉ የተባሉትን አባባሎች በሙሉ ፣ በ11 ርዕሰ ጉዳይ እና በ9 የስሜት ምድቦች ለፍለጋ አምቻችቶ አቅርቦልናል፡፡
ጥልቀት ባለው ዕውቀታቸው እና ለግጥም በተስተካከሉ አጫጭር ስንኞቻቸው ፣ ለፅሁፋችን ጣፋጭነት ዛሬውኑ ለመጠቀም ዝግጁ ናቸው።
ግጥምጥም አፕ ፣ ስድስት የፍለጋ መተግበሪያዎችን ያካትታል (3 ፍለጋ በቃላት እና 3 ፍለጋ በምሳሌያዊ አባባሎች) -
“ፍለጋ በቃላት”ን እንመልከት -
1. "ሁሉም ቃላቶች" ማውጫ - ነጠላ ፊደልን በማስገባት (ከክፍያ ነፃ) -
ተጠቃሚው በፍለጋ ሳጥኑ ነጠላ ፊደል (የቃል ማለቂያን ሆሄ) በማስገባት እና “ሁሉም ቃላቶች” የሚለውን በመጫን ፣ በዚህ ፊደል የሚያልቁትን ቃላት በዝርዝር ማግኘት ያስችለዋል፡፡
2. "ሁሉም ቃላቶች" ማውጫ - ቃላትን በማስገባት (ከክፍያ ነፃ) -
ተጠቃሚው በፍለጋ ሳጥኑ ቃል በማስገባት እና “ሁሉም ቃላቶች" የሚለውን በመጫን ፣ ከዚህ ቃል ጋር በላቀ የሚገጥሙትን ይዘረዝርለታል። ይህ የግጥምጥም አልጎሪዝምን የሚጠቀም ፍለጋ ፣ ማለቂያ ፊደልን ማመሳሰል ብቻ ሳይሆን ፣ ከማለቂያ አንድ ወደ ውስጥ የሚገኙትንም ፊደላት ድምፅ በማስተዋልም ነው።
3. ቃላቶች በፊደል ቁጥር ፍለጋ - "ባለ 2-ፊደል" እስከ "ባለ 5-ፊደል" ያላቸውን ቃላት ማውጫ -
ማንኛውም ቃል በማራኪነቱ የሚገጥመው ፣ ከሌላ ተመሳሳይ ፊደል ቁጥር ካለው ቃል ጋር ነው።
ይህ የግጥምጥም መሳሪያ ፣ ከ50ሺ በላይ የያዘውን ቃላቶች በ2 - 5 ፊደል ይዞታቸው ለያይቶ በድምፀ ልኩ የሚዘረዝር ነው።
ለምሳሌ ፣ ”እፍ” ለሚለው እንደሆነ የሚገጥም ቃል የምንፈልገው ፣ በ2-ፊደል ስር በ“ፍ“ ከሚያልቁት በከፊሉ የሚከተሉትን እናገኛለን - ጫፍ ፣ ፃፍ ፣ ሽፍ ፣ ቅፍ ፣ ትፍ ፣ ክፍ ፣ ድፍ ፣ ግፍ ፣ ወዘተ፡፡
በፊደል ቁጥር ፍለጋ የምናገኘው ውጤት ፣ ለጆሮ ምቾትና ለትርጉም እርካታችን ምንጭ ሊሆነን እንደሚችል በቀላሉ የምናየው ነው፡፡
ስንኞችን በድምፅ ሜትር (ርዝማኔ እና እጥረት) በመቆጣጠርም ፣ ይህ ለግጥም ግምባታ ብሎኬት ነው።
ተጠቃሚው ፣ የሚፈልገውን ቃል ወይም የቃል ማለቂያን ፊደል በፍለጋ ሳጥኑ አስገብቶ ፣ “ባለ 2-ፊደል” እስከ “ባለ 5-ፊደል” የቀረቡትን አማራጮች በመጫን ፣ ተመሳሳይ የፊደል ብዛት ያላቸውን የሚገጥሙ ቃላት ያበረክታል፡፡
ፍለጋ በ"ምሳሌያዊ አባባሎች”ን እንመልከት -
4. "ሁሉም ምሳሌያዊ አባባሎች" ማውጫ -
ተጠቃሚው ፣ ለግጥም የሚፈልገውን ቃል ወይም ማለቂያ ፊደል በፍለጋ ሳጥኑ አስገብቶ "ሁሉም ምሳሌያዊ አባባሎች" የሚለውን ማውጫ በመጫን ፣ ከ5ሺ ምሳሌያዊ አባባሎች በተፈለገው ፊደል የሚያልቁትን ለይቶ ይዘረዝራል፡፡
5. “ምሳሌያዊ ምድቦች" ማውጫ -
ይህ ማውጫ ፣ ከ5ሺ በላይ ምሳሌያዊ አባባሎችን በሚከተሉት 11 ርዕሰ ጉዳይ እና 9 የስሜት ሚዛነ ፈርጆች ለይቶ ያወጣል።
በአስራ አንድ ርዕሰ ጉዳይ -
1. መንፈሳዊነት / እውነታ ፣
2. እውቀት / መፍትሄ ፣
3. በረከት ፣
4. ጋብቻ / ቤተሰብ ፣
5. ዝምድና/ ወዳጅነት ፣
6. ሀይማኖት ፣
7. ንጉሳዊነትና ማንነት ፣
8. ሞት ፣
9. ጭንቀት / ሂደት ፣
10. ስህተት / ሞኝነት / ትችት ፣ እና
11. ድህነት / ችግር ፣ ናቸው።
በዘጠኝ የስሜት ሚዛነ ፈርጆች - (ለምሳሌ ድፍረትን የሚመለከቱ አባባሎች እንደሆን የምንፈልገው ፣ ስለ ፍራቻ የሚገልፁትንም ማየቱ ይረዳል)።
1. ድፍረት - ፍራቻ ፣
2. ፍቅር - ጥላቻ ፣
3. ትእግስት - ንዴት ፣
4. ደስታ - ሀዘን ፣
5. ጉጉት - መዘግነን ፣
6. ተስፋ / እምነት - ጥርጥር ፣
7. ውስጠ ኩራት - ሀፍረት ፣
8. ቅንነት - ቅናት ፣ እና
9. ምስጋና - ፀፀት ፣ ናቸው።
ተጠቃሚው ፣ ግጥም የሚፈልግለትን ቃል ወይም ማለቂያ ፊደል በፍለጋ ሳጥኑ አስገብቶ "ምሳሌያዊ ምድቦች" የሚለውን ማውጫ በመጫን ፣ ወደ ምድቦቹ አማራጭ ገፅ ይሄዳል። ከዛም ፣ የሚመርጠውን የምድብ ሳጥን አመልክቶ "ይፈልጉ" የሚለውን ይጫናል።
የዚህ ፍለጋ ውጤት ፣ ምልክት በተደረገባቸው ምድቦች ስር ከሚገኙት አባባሎች ውስጥ ፣ በተፈለገው ፊደል የሚያልቁትን ይዘረዝራል።
ከአንድ በላይ ምድብ ሳጥን ካመለከትን ፣ በተመረጡት ምድቦች በጋራ የሚገኙትን ምሳሌያዊ አባባሎቸ እየፈለግን ነውና ፣ የውጤቱ ዝርዝር እየጠበበ ይመጣል። ይህ ፣ የምንሻውን ጭብጥ በበለጠ ለማነጣጠር ያስችለናል።
6. “ቃል-አዘል ፍለጋ" ማውጫ -
የፈለግነውን ቃል በውስጣቸው የያዙትን ምሳሌያዊ አባባሎች በሙሉ የሚዘረዝርልን መሳሪያ ነው። ይህ ያሰብነውን ጭብጥ በተሻለ ለማጥመድ ይረዳናል።
ተጠቃሚው ፣ የሚፈልገውን ቃል በፍለጋ ሳጥኑ አስገብቶ “ምሳሌያዊ ምድቦች" የሚለውን ይጫናል። ከዛም “ቃል-አዘል ፍለጋ" የሚለውን ሳጥን ምልክት አድርጎ “ይፈልጉ"ን ይጫናል፡፡
የዚህ ውጤት ዝርዝር በማለቂያ ፊደል የተወሰነ አይደለም።
ምልክት የተደረጉ ሌሎች ሳጥኖች ካሉ ፣ በምድቦቹ ስር በጋራ የሚገኙትን እየፈለግን ስለሆነ ፣ የውጤቱ ዝርዝር እየጠበበ ይመጣል።
የግጥምጥም 5ስቱ መተግበሪያ እነዚህ ነበሩ።
አንዳንድ መረጃ -
- የአማርኛ መተየቢያው (ኪቦርድ) ያስፈልጎት እንደሆን ፣ በፍለጋ ሳጥኑ ውስጥ ምልክቱን ያገኙታል፡፡
- አጭሬ ግጥም (4 - 8 ስንኝ) በቀላሉ ልንፅፍላቸው የምንችለው አጋጣሚዎች -
- ደስታን ለመግለፅ - ለሰርግ ፣ ለልደት፣ ለምርቃት ወይም የበኩር ልጅ ሲወለድ ፣
- በቡድን - በቤተሰብ ፣ በባልንጀራ ወይም በስራ አጋር መካከል ተሁኖ ፣ ለአንዳች ኩነት አንድላይ ማድመቂያ ፣
- በማህበራዊ ሚድያ እራስን ለመግለፅ ፣
- ለዘፈን ግጥም (ሊሪክ) - ራፕ ለማድረግ ፣ ለማዜም ወይም ለአምልኮ ፣
- ለምስጋና እና ይቅርታ መግለጫ ፣
- በሀዘን ጊዜ ለራሰ ወይ የማፅናኛ ድጋፍ ለመሆን ፣
- ፍቅርን ለመግለፅ ፣ ከእጮኛ ግንኙነትን ለማዳበር ወይ ለጋብቻ እጅ ጥያቄ ፣
- ለመድረክ ንግግሮች ማጀቢያ ፣
- ከማንኛውም ፅሁፍ ውስጥ (ስራ ሆነ ት/ቤት) ቀልቀል ለማድረግም ይሆናል።
የግጥምጥም ራእይ -
በስነ ቃል / በስነ ፅሁፍ ዙሪያ የፈጠራ ክህሎትን በሰፊው ለማሳደግ እና ትርጉም ላለው ማህበረሰባዊ ለውጥ (ግንኙነት) ድጋፍ ለመሆን ነው፡፡
ግምገማ -
የግጥምጥም አገልግሎትን ከወደዱት ፣ በ5 ኮከብ ሆነ በሌላውም ደረጃ ድጋፍ በፍቅር እንቀበላለን፡፡